አማራ ክልል → ሰሜን ወሎ ዞን → ጋሸና ከተማ አስተዳደር → ጋሸና ከተማ
የጋሸና ከተማ አስተዳደር ጅኦግራፊያዊ አቀማመጥ
እድገቶች
1. የመንገድ እና መሠረተ ልማት ልማት
ከተማዋ ከአካባቢ ከተሞች ጋር የሚያገናኝ መንገድ እየተሻሻለ ነው
የዋና መንገዶች እና የውስጥ መንገዶች (ኮብል ወይም አስፋልት) በመጨመር ላይ ናቸው
የመጓጓዣ አገልግሎት (ባስ፣ ሚኒባስ) እየተሻሻለ ነው
ይህ ንግድን እና ግንኙነትን ያበረታታል

ከተማዊ እድገት መጨመር
አዳዲስ መኖሪያ ቤቶች እየተገነቡ ናቸው
ንግድ ቤቶች (መደብሮች፣ ሆቴሎች፣ ካፌዎች) እየበዙ ናቸው
ገበያዎች እና ንግድ እንቅስቃሴ እየጨመረ ነው
ይህ ከተማዋን ከመካከለኛ ደረጃ ወደ ከፍ ያለ ከተማ ለመድረስ ያግዛል
የህዝብ አገልግሎት መሻሻል
ትምህርት ቤቶች በመጨመር
ጤና አገልግሎቶች እየተሻሻሉ
ውሃ እና ኤሌክትሪክ አቅርቦት በቀስታ እየተሻሻለ
የህዝብ አገልግሎት መሻሻል
ትምህርት ቤቶች በመጨመር
ጤና አገልግሎቶች እየተሻሻሉ
ውሃ እና ኤሌክትሪክ አቅርቦት በቀስታ እየተሻሻለ
ጋሸና ከተማ
December 1, 2021
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ወሎ ዞን ጋሸና ከተማ አስተዳደር አነስተኛ ከተማ ናት ጋሸና፡፡ ከተማዋ ደቡብ ጎንደርን በስተምእራብ፣ ወልዲያን በስተምስራቅ፣ ላሊበላን በስተሰሜን እና ወገልጤናን በስተደቡብ የምታዋስን ስትራተጂክ ከተማ ናት፡፡
አሁን ባለው መረጃ መሰረት በከተማዋ በግዜያዊነት የሚኖሩ ዜጎችን ጨምሮ ወደ 22 ሺህ የሚጠጋ ነዋሪ ይኖርባታል፡፡ ይህች ተራራማ በሆነ ቦታ ላይ የተቀለሰች ከተማ ደጋማ የሆነ የአየር ንብረት ሲኖራት፣ ከባህር ጠለል በላይ በ2977 ሜትር ከፍታ ላይ ትገኛለች፡፡
ከተማዋ ከጂኦግራፊያዊ አቀማመጧ እና መልካምድሯ ጋር በተያያዘ ወሳኝ ስፍራ የሆነችበትም ምክንያትም የስድስት በሮች መተላላፊያ መስመር በመሆኗ ነው። ይህም በስተምእራብ ወደ ጎንደር፣ በስተምስራቅ ወደ ወልድያ፣ በስተደቡብ ወደ ወገልጤና (ደላንታ) ይገባና ከወገልጤና ወደ ደሴና ወደ ምእራብ ውሎ (ተንታ፣ አቀስታ፣ ቦረና) ያስገባል። በተጨማሪም በስተሰሜን በኩል ወደ ላሊበላ፣ አይና ቡግና፣ ወደ ሰቆጣና ወደ ኮረም (ትግራይ) ያስገባል። ይህም ጋሸናን የኮረም፣ የሰቆጣ፣ የወልድያ፣ የጎንደርና የደሴ መግቢያ በር በመሆንዋ ለወታደራዊም ይሁን ኢኮኖሚዊ ጠቀሜታዋ የጎላ ነው።
ይህንም በዝርዝር ለማየት፣ ከተማዋ አዋሳኝ የትራንስፖርት አማራጭ የሆነችበትም ምክንያት ለማየት ያክል ከወልድያ ወደ ጎንደር የሚወስደውን ዋና የአስፓልት መንገድ፣ ከጋሸና ወደ ወገልጤና የሚወስደው መንገድም ገርማሜ ሲደርስ በስተምስራቅ የደሴን አስፓልት በስተምእራብ ደግሞ የወረኢሉን ዋና አስፓልት መዳረሻ በመሆኑ ነው፡፡ በተለይም ከጋሸና ተነስቶ በላሊበላ መስመር ላስታን፣ አይና ቡግናን፣ ግደንን፣ እልፎ ቤላ ሲደርስ በስተሰሜን ሰቆጣን በስተምስራቅ ደግሞ ኮረምን የሚያዋስን መንገድ አለው፡፡
የሰቆጣን መስመር ይዘን ስንሄድም፣ እስከ አግቤ/ አቢ አዲ (ትግራይ) ድረስ የሚያስኬድ እና ዋናውን የአስፓልት መስመር የሚያዋስን መንገድ የያዘች ከተማ ናት፡፡