04-04-2026 22:55pm
የጨረታ ማስታወቂያ
1 የጨረታ ዙር 1 እና 2ኛ 2. የጨረታው አይነት መደበኛ የጋሸና ከተማ መሬት ጽ/ቤት የከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ቡድን የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ 721/2004 አንቀጽ 8 ንዑስ አንቀጽ 1 በፊደል ተራ ቁጥር ከ ሀ እስከ ሠ በተዘረዘረው መሰረት ለመኖሪያ የተዘጋጁ ቦታወቹን በመደበኛ ጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል። በመሆኑም መጫረት የሚፈልግ ማንኛውንም ሰው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን (ከ24/7/2018) ዓ.ም ጀምሮ የቦታውን ዝርዝር መረጃ እና የጨረታ ሰነድ የማይመልስ 300/ሶስት መቶ/ብር በመክፈል ለጋሸና ከተማ መሬት ጽ/ቤት ውስጥ ቤሮ ቁጥር 5 በመምጣት ዘወትር በስራ ሰዓት ⌚ መግዛት የሚችል መሆኑን እናሳውቃለን: ቦታው የሚገኝበት አድራሻ ጋሸና ከተማ አስተዳደር በቀበሌ 01 ነው
