የጋሸና ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ፅ/ቤት
13-07-2026 17:32pmየጋሸና ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ፅ/ቤት የ2017 በጀት አመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማና የ2018 በጀት አመት የእቅድ ትዉዉቅ መድረክ ከከተማ አስተዳደሩ ጠቅላላ አመራር እና ከተቋሙ ጠቅላላ ሰራተኛ ጋር የዉይይት መድረክ ተካሄደ።
መስከረም:-25/2018ዓ.ም
ጋሸና!! የመድረኩን የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የጋሸና ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ፀጋ ዉቤ ሲሆኑ በንግግራቸዉ ተቋሙ በ2017 በጀት አመት ጥሩ አፈጻጸም በማምጣት እና ህዝብን ተጠቃሚ የሚያደርግ ስራ ሰርቶ በዞን ካሉት ከተማ አስተዳደሮች 1ኛ ደረጃ በመዉጣት የዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል ያሉ ሲሆን ለ2018 በጀት አመትንም ይህንኑ ደረጃ ለማስጠበቅ ሁሉም የስራ ቡድኖች ተግባራቶችን በዉጤታማነት መፈጸም ይጠበቃል ሲሉ ገልፀዋል። አክለዉም ይህ ተቋም በይበልጥ ለከተማ አስተዳደሮች የጀርባ አጥንት ስለሆነ ሁሉም አመራር ለተቋሙ አጋዥ መሆን እንደሚጠበቅ አሳስበዋል።
የመድረኩን ሰነድ የጋሸና ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ፅ/ቤት ዋና ስራ - አስኪያጅ አቶ አወቀ አለሙ ያቀረቡ ሲሆን በ2017 በጀት አመት የነበሩ ጥንካሬዎችን እና ድክመቶችን ገላጭ በሆነ መንገድ በማመላከት ለቀጣይ በጀት አመት ጥንካሬዎችን ይበልጥ በማጠናከር የነበሩ ክፍተቶችን በማረም የተሻለ ስራ መስራት እንደሚገባ ገልፀዋል።
የዉይይት መድረኩን የጋሸና ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ፀጋ ዉቤ ፣ የጋሸና ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ ብርሃን መክብብ እና የጋሸና ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ፅ/ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አወቀ አለሙ በጋራ መርተዉታል።
ይህ መረጃ 14 ጊዜ በተለያዩ ሰዎች ታይቷል ---) (----
ይህንን መረጃ ከታች ባሉት 👇 👇 👇 ሚዲያወች በመጫን Share..
